ዜናዎች

የአካባቢው ማኅበረሰብ ወጣቶች በፋብሪካው የአገዳ ዘር ዝግጅት ሥራ ተሳተፉ
ከአካባቢው ማህበረሰብ የተውጣጡ ወጣቶች አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ እያከናወነ ለሚገኘው የአገዳ ዘር ዝግጅት ስራ የጉልበት ድጋፍ አደረጉ፡፡
ከቡኖ በደሌ ዞን ዳቦሐና ወረዳ ቀርከሃ ዲዴሳ እና ከምስራቅ ወለጋ ዞን ጅማ አርጆ ወረዳ አቦቴ ዲዴሳ ቀበሌ የተውጣጡ 337 ወጣቶች እና የቀበሌዎቹ አመራሮች የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በ2017 በጀት ዓመት እያከናወነ ለሚገኘው የሸንኮራ አገዳ ተከላ ሥራ ድጋፋቸውን ለማሳየት ግንቦት 26 እና 28 ቀን 2017 ዓ.ም የአገዳ ዘር በማዘጋጀት ተሳትፈዋል፡፡
የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ምርት በማቆሙ ምክንያት በአካባቢው ያለው የስራ እድል መቀዛቀዙ በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ መሆኑን የገለጹት በዘር አገዳ ተከላ ሥራው የተሳተፉት ወጣቶች የስራ አጥነት እንዲቀረፍ ፋብሪካው ጉልህ ድርሻ ያለው በመሆኑ ፋብሪካው ወደ ምርት እንዲመለስ የሚያደርገውን ጥረት በመደገፍ በቀጣይም ከፋብሪካው ጎን በመሆን ድጋፋቸውን አጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን መግለጻቸውን ከፋብሪካው የተላከው መረጃ አመልክቷል፡፡ በቀጣይም በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በኩል የፋብሪካውን የአገዳ ተከላ ስራ የመደገፍ መርሐግብር መያዙንም ዘገባው አያይዞ ገልጿል፡፡
admin
0