• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
Uncategorized
በአምባሳደር ግርማ ብሩ ሰብሳቢነት የሚመራው የግሩፑ የሥራ አመራር ቦርድ የዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ግንባታን ጎበኘ

በአምባሳደር ግርማ ብሩ ሰብሳቢነት የሚመራው የግሩፑ የሥራ አመራር ቦርድ የዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ግንባታን ጎበኘ

በክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራው የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሥራ አመራር ቦርድ የግሩፑን የወደፊት የዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ የግንባታ ሂደትን ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የህንጻ ግንባታው ኮንትራክተር የቲኤንቲ ኮንትራክሽንና የአማካሪው ድርጅት ባለሙያዎች የግንባታውን ሂደት በተመለከተ ለሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢው አምባሳደር ግርማ ብሩና ለአባላቱ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ባለሙያዎቹ በገለጻቸው የሕንጻው የመዋቅር ሥራ 90 በመቶ የአጠቃላይ ግንባታው ሥራ ደግሞ 70 በመቶ መድረሱን ጠቅሰው 27ኛ ወለል ላይ ከደረሰው የመዋቅር ሥራው ጎን ለጎን የማጠናቀቂያ ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

ለሕንጻው ማጠናቀቂያ የሚውሉ የኤሌክትሮሜካኒካል ግብአቶች በሙሉ በሙሉ ከውጭ አገር መግባታቸውንና ግብአቶቹን ለመግጠም ዝግጅቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውንም ባለሙያዎቹ አስረድተዋል፡፡

በጉብኝቱ የግሩፑ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ዋና አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ የግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ግንባታ በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቁመው ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ አጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ርብርብ እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ ከሥራ አመራር ቦርድ አባላት በተጨማሪ የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባና የማነጅመንት አባላት ተሳትፈዋል፡፡