ዜናዎች

በዋና ሥራ አስፈጻሚው የተመራው ልዑክ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ጉብኝት አካሄደ
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በክቡር አቶ ወዮ ሮባ የተመራውና የግሩፑ ከፍተኛ አመራር አባላትን ያካተተው ልዑክ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም በመገኘት የሸንኮራ አገዳ ማሳ፣ የሸንኮራ አገዳ ዝርያ የማላመድ ሥራዎችን፣ ለተከላ የተዘጋጁ ማሳዎችን እንዲሁም የአገዳ ቆረጣና አያያዝ የመንገድ ሥራዎችንም ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡
በዚሁ ወቅት ክቡር ዋና ስራ አስፈጻሚው ኢንዱስትሪ ግሩፑ በሰው ኃይልም ሆነ በግብዓት ለፋብሪካው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
ፋብሪካው ለ2016 የያዘውን የአገዳ ተከላ ዕቅዱን ለማሳካት ተግቶ መሥራት እንደሚጠበቅበትም ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚው ያሳሰቡት፡፡
በተጓዳኝ ልማት በ32 ሄክታር መሬት ላይ ተዘርቶ በመሰብሰብ ላይ ያለው የበቆሎ ምርትም በልዑኩ ተጎብኝቷል፡፡

admin
0