ዜናዎች

ርዕሰ መስተዳድሩና ልዑካቸው በፋሪካው ጉብኝት አደረጉ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እና የልዑካን ቡድናቸው ሚያዚያ 18 ቀን 2016ዓ.ም በኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሦሥት ስኳር ፋብሪካ ጉብኝት አደረጉ፡፡
በጉብኝቱ ላይ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንደስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ፣ የግሩፑ የሰርስ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርኃም ደምሴ እንዲሁም የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሦሥት ስኳር ፋብሪካ የሥራ መሪዎች ለርዕሰ መስተዳድሩና ለልዑካን ቡድናቸው ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ እና ልዑካቸው ፋብሪካው በማልማት ላይ የሚገኘውን የሸንኮራ አገዳ ልማት፣ በኦሞ ወንዝ ላይ የተገነባውን ግድብ (ኮፈር ዳም) እና ፋብሪካውን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራውና የክልሉን ከፍተኛ አመራሮች ያካተተው ልዑክ ከኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች ጋር የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሦሥት ስትሪንግ ኮሚቴ ማጠናከር በሚቻልበትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በፋብሪካው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
admin
0




