ዜናዎች

የግሩፑ ህግና ኢንሹራንስ መምሪያ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ የቀረበ ክስን በፍ/ቤት ውድቅ አስደረገ፡፡
ለከሰም ስኳር ፋብሪካ አገዳ ሲያቀርብ የቆየው አሚባራ እርሻ ልማት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስኳር ፋብሪካው በመበላሸቱ ምክንያት አገዳ ባለመነሣቱ ብር 1.2 ቢሊዮን (አንድ ቢሊዮን ሁለት መቶ ሚሊዮን) የፍትሐብሔር ክስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መስርቶ ግሩፑ ባደረገው ክትትል ውድቅ መደረጉን የግሩፑ ህግና ኢንሹራንስ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፋሲል ገ/ማርያም ገልፀዋል፡፡
ክሱ ለሁለት አመት ክትትል ሲደረግበት የቆየ ሲሆን በግሩፑ በኩል የቀረበው ክርክር ሙሉ እርሻውን ለመግዛት ስምምነት አለመኖሩን፣ አገዳ የሚሸጠው ሻጩ ቆርጦ ሚዛን ቤት ሲያቀርብ ብቻ እንደሆነ እና ፋብሪካው የቀረበለትን አገዳ በሙሉ ማንሣቱን እና ሌሎች ዝርዝር ክርክሮችን በማቅረብና የፅሁፍ እና ጉዳዩን የሚያውቁ የሰው ማስረጃዎችን በማሠማት ክሱን ውድቅ ማስደረግ ተችሏል፡፡
በመጨረሻም አቶ ፋሲል ለክሱ ውጤታማነት የግሩፑ ከፍተኛ አመራር አካላትና ባለሙያዎች እንዲሁም የፍትሕ ሚ/ር ዐ/ህግ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡
admin
0