• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
ዜናዎች
በበጀት ዓመቱ የመንግስት የአስር ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

በበጀት ዓመቱ የመንግስት የአስር ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አመራር አባላትና ሰራተኞች በበጀት ዓመቱ የአስር ወራት የመንግስት የዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ሐሙስ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት አድርገዋል፡፡

ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የአዲስ አበባ መስተዳድር ፍትህ ቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ የመንግስት የአስር ወራት የዕቅድ አፈጻጸም በግሩፑ የማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ በአቶ ታፈሰ አሰፋ አማካይነት ዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ ነው ውይይት የተደረገበት፡፡

በዚሁ የውይይት መድረክም የ2016 በጀት ዓመት የአስር ወራት ዋና ዋና የዕድገት አመላካች የሆኑት የግብርና፣ የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ዘርፎች እንዲሁም የሌሎች ዘርፎች አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

የአምራች ዘርፉን አፈፃፀም በተለይም ደግሞ የስኳር ዘርፉ ያለበት ሁኔታም በውይይቱ ወቅት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በአገር ደረጃ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተመዘገበው ውጤት የስኳር ኢንዱስትሪ ያበረከተው አስተዋጽዖ የማይናቅ በመሆኑ ሠራተኛው በ2017 በጀት ዓመት ለማሳካት ለታቀዱ ተግባራት ስኬት የሚጠበቅበትን እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል፡፡

የመንግስት የ2017 በጀት ዓመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችም በውይይቱ ላይ የቀረቡ ሲሆን በ2016 እንደሚመዘገብ የሚጠበቀውን የ7.9 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት በ2017 በጀት ዓመት ወደ 8.3 በመቶ ለማሳደግ ማቀዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ የመንግስት የአስር ወራት የዕቅድ አፈጻጸምና ተቋሙን የተመለከቱ ጉዳዮች በቀረቡበት የውይይት መድረክ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ተሰጥቶ መግባባት ላይ በመድረስ የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *