ዜናዎች

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሠራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይን ጎበኙ
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሠራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን ሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይን ጎበኙ፡፡
የግሩፑ ሠራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን ሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይን የጎበኙት ጥቅምት 13 ቀን 2016ዓ.ም ነው፡፡
ሀገር አቀፉ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይ ጎብኚዎች ኢትዮጵያን ምቹ መዳረሻ የሚያደርጓትን ምክንያቶች በናሙና እንዲያዩ ዕድል የሰጠ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
በአውደ ርዕዪው የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሥፍራዎች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የኪነ-ጥበብ ኃብቶችና የዘርፉ ተዋንያን አገልግሎቶች ለዕይታ ቀርበዋል።
admin
0





